logo
Sign in Sign up
icon English
  • icon English
  • icon Español
  • icon Français
  • icon Deutsch
  • icon Portugués
  • icon Pусский
  • icon 中國語
  • icon 日本語
  • icon Netherlands
  • icon Indonesia
logo
icon English
  • icon English
  • icon Español
  • icon Français
  • icon Deutsch
  • icon Portugués
  • icon Pусский
  • icon 中國語
  • icon 日本語
  • icon Netherlands
  • icon Indonesia
  • The New Life Mission
  • Contact Us
  • Privacy Policy
  • Terms and Conditions

“መዝገብህ ባለበት ልብህ ደግሞ በዚያ ይሆናልና።”(ማቴ6፥21)

mesfin2010 Mesfin
· Ethiopia · 527 day
views 3278
comments 0

 መዝገብህ ያለው ዬት ነው? ምድር ላይ ነው ወይስ ሰማይ ላይ ነው? ስለእግዚአብሔር ጽድቅ፣ ስለእግዚአብሔር መንግስት፣ ስለደኅንነትህ፣...... እንቅልፍ ነስቶህ ያውቃል❓ በውኑ በእግዚአብሔር ቃል ታምናለህ? በትክክል መንግስተ ሰማይ እንዳለና በትክክል ገሃነም እንዳለ ታምናለህ? ኃጢአት ያለበት ዘላለማዊ ፍርድ በሆነው በገሃነም እሳት ከዘላለም እስከ ለዘላለም እየተቃጠለ እንደሚኖር ታምናለህ? ጌታ ኢየሱስ አንተን ከገሃነም ሊያድንህ በውኃና በደም እንደመጣ(1ዮሐ5፥6) ታምናለህ? ኢየሱስ በውኃና በደም መጣ ማለት ምን ማለት ነው? የእግዚአብሔር ጠላት የሆነው ሰይጣን አንተን በኃጢአት ጥሎ ለዘላለም ሞት ያዳረገህ መሆኑን ታምናለህ? አንተ እዚህ ምድር ላይ ኃጢአተኛ ሆነህ የተወለድክ ከዚህ ምድር እስከሚትለይ ኃጢአትን የሚታደርግና በኃጢአትህ የዘላለምን ሞት ለመሞት የታጨህ ጎስቋላ ሰው መሆንህን ታምናለህ? የእግዚአብሔርን መንግስት እንዴት ነው የምገባው? ብለህ ለዚያ ሰርተህ ታውቃለህ❓ እዚህ ጋር "ሰርተህ" ስልህ አስራትና በኩራት፣ ምጽዋት፣ ጾምና ጸሎት፣ ለድሆች መስጠት፣ በሆነ ክርስትና ኃይማኖት ስር ስለመጠለል፣...... እያልኩህ አይደለም። ምንም ስለኃጢአትና ስለጽድቅ፣ ስለእግዚአብሔር መንግስት፣...... ግድ የማይልህና የማያሳስብህ ልብህ በምድራዊ ነገር ከብዶና ደንዝዞ ስላለ ነው። ልብህ ምድር ላይ ያለው መዝገብህ ምድር ላይ ስላለ ነው። ይህ ማለት አንተ ኃጢአተኛ ሆነህ መወለድህን የማታምንና ከኃጢአትህ በአንድ ጊዜ መዳን የማትፈልግ ነህ ማለት ነው። ስለዚህ አንተ ወደ ገሃነም ትጣላለህ ማለት ነው። ገሃነም ሲባል ምንም የማትፈራው ምድራዊ ስለሆንክ ነው። ምድራዊ ነህ ማለት ከዱር አራዊት፣ ከእንስሳትና ከእጽዋት አትሻልም ማለት ነው። አሁንም ተንቀሳቀስ ገሃነም ከፊትህ አለ፤ ገና ወደ ገሃነም አልገባህም፣ ዕድልና ጊዜ አለህና ካለህበት ከክፉ መንገድ ተመለስና የእውነትን መንገድ ተከተል። ይህ የእውነት መንገድ የእግዚአብሔርን ጽድቅ የሚሰብከው የውኃውና የመንፈሱ ወንጌል ነው። ወደዚህ ወንጌል ተመለስ! ያኔ የእግዚአብሔርን መንግስት ትወርሳለህ።(ዮሐ3፥5) www.nlmethiopia.com 

-

t.me/tobebornagain 

IMG_20231125_083717_386.jpg
  • Prev
    میری نجات کی گواہی
  • Next
    The Wisest Way of Life
mesfin2010
ETH

Mesfin(Mesfin Berhanu Ubba) ∙Ethiopia

የውኃውና የመንፈሱ ወንጌል ለዓለም ሁሉ

Comments 0
mesfin2010
0/2000
Links
The New Life Mission Contact Us Privacy Policy Terms and Conditions
The New Life Mission Logo

Copyright © 2020 by The New Life Mission